ፕሮግራም ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሶፍትዌሮችን ከድህረ-ገጽ ማውረድ እና በኮምፒውተራችን ላይ መጫን ይኖርብናል ነገር ግን ሁሉም ፕሮግራሞች ፕሮግራም ለመጀመር ሶፍትዌር መጫን አይጠይቁም። ለምሳሌ ያህል በHTML, CSS, Javascript ፕሮግራም ለመጀመር ከፈለጉ የፅሁፍ ማዘጋጃ Notepad፣ TextEdit ወይም web browser ብቻ ያስፈልገናል።
ፕሮግራም ለማድረግ የሚከተሉትን የፐሮገራም ቋንቋዎች ከዚህ ቀጥሎ ከነድህረ-ገጽ በማውረድ መጠቀም እንችላለን፡-
Ruby፡- የሩቢ አዲስ ስሪትን ጨምሮ ቆየት ያሉትንም ለማግኘት ይህን ድህረ-ገፅ መጠቀም እንችላለን https://www.ruby-lang.org/en/downloads/
Python፡- ብዙ ኮምፒዩተሮች ቀደም ሲል Python የተገጠመላቸው ቢሆኑም ነገር ግን በPython ፕሮግራም ከመጀመርዎ በፊት የቅርብ ጊዜውን ስሪት መጫን ያስፈልግዎት ይሆናል። የቀደሙትንም ስሪት ለማግኘትም ያስችለናል። ለማውረድ ይህን ይጫኑ Download Python | Python.org
Java:- የጃቫ ሶፍትዌር ከማውረዳችን በፊት ኪት (Software Development Kit) መጫን ያስፈልጋል። በጃቫ ውስጥ ፕሮግራም ለመጀመር በሚቀጥለው ድህረ-ገጽ በመግባት Java Downloads | Oracle በማውረድ መጠቀም ይቻላል።
PHP እና MySQL፡- ይህ በኮምፒውተር ፋንታ በሰርቨር ላይ የሚጫን ሲሆን። ይሁን እንጂ PHP እና MySQLን በኮምፒዩተርዎ ላይ ለመጠቀም፣ ለመፈተሽ እንደ Apache ያሉ የሰርቨር ሶፍትዌሮችን ማውረድ እና መጫን ያስፈልገናል። WAMPን ጨምሮ በርካታ የሶፍትዌር አጋዥ ጥቅሎች አሉ እና በአንድ ፕሮግራም ውስጥ የሚያስፈልገንን ሁሉ ያላቸው ናቸው።
ፕሮግራም ለማድረግ የምንጠቀምባቸው መሰረታዊ ከሚባሉ ቋንቋዎች እነዚህ ሰሆኑ ስለ አጫጫናቸው እና አጠቃቀማቸው በሚቀጠለው የምናያቸው ይሆናል።


1 Comment
hola