ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ?
ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ በተደጋጋሚ በሚሰሩበት ጊዜ ትክክለኛነትን ለመጨመር እና የተማሩ ውሳኔዎችን በፍጥነት ለመወሰን ጠቃሚ ነው ። የበለጠ ፈጠራ እና እርካታ ባለው ስራ የበለጠ ለማተኮር ጊዜን በመቆጠብ የሰራተኛውን እርካታ ይጨምራል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ, አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምን እንደሆነ እና እንዴት እንደሚሰራ እንመረምራለን, የተለያዩ የ AI ዓይነቶች ይገኛሉ, እንዲሁም ብዙ ጥቅሞችን እና ጉዳቶችን እንመረምራለን።
ሠው ሰራሽ ዕውቀት (Artificial Indigence) ምንድን ነው?
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በማሽኖ የሚታየው የማሰብ ችሎታ ነው። ብዙውን ጊዜ የማሽን መማር ተብሎ የሚጠራው AI ማሽኖች ከተሞክሮ እንዲማሩ እና ሰው መሰል ተግባራትን እንዲያከናውኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሲሆን።
ሰው ሰራሽ እውቀት ስንል አሳቢ የሆኑ ማሽኖች የሚመረቱበት እና ሶፍትዌር የሚሰሩበት እና የሚጠኑበት ዘርፍ ነው። የዘርፉ ዋና ዋና ተመራማሪዎች እና መፅሃፍት ዘርፉን ሲገልፁ “አሳቢ ነገሮችን የሚሰራ እንዲሁም የሚያጠና” ብለው ይገልጹታል። አሳቢ ወይም አዋቂ ነገር የሚለው አገላልፅ የሚያመለክተው ስላሉበት ካባቢ ሁኜታ ለመረዳት መቻልን እና ከዚሁ መረዳት በመነሳት (ለመኖር የሚያስችል) ተመጣጣኝ ድርጊት ለማድረግ መቻልን። ይህን የቴክኖሎጂ ዘርፍ ስያሜውን ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1955 የተጠቀመበት ጆን ማካርቲ የተባለ ተመራማሪ ዘርፉን ሲገልፅ “አሳቢ ወይም አዋቂ ማሽኖችን ለመስራት የሚደረግ ሳይንስና ምህንድስና” ይለዋል።


AIን በመጠቀም ኮምፒውተሮች ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃን በፍጥነት፣ ተደጋጋሚ ሂደት እና የሂሳብ ስሌቶችን/ቀመሮችን በማጣመር እራሳችው ባህሪያትንና ነገሮች እንዲረዱና ምላሾችን እንዲሰጡ ያግዛቸዋል። የAI ዝንባሌው ከእውኑ አልም ጋር ተስማሚ ነገሮችን ለመፍጠር የሂሳብ ስሌቶችን እና ታሪካዊ መረጃዎችን በመሰበሰብ ተስማሚ የሆነ ውጤቶችን ና ትንበያዎችን መስጠት ይጀምራሉ። ዘርፉ ባጠቃላይ የረቀቀና እና ገና ሁሉን አቀፍ ያልሆነ (ስፔሻላይዝድ ያልሆነ) መሆኑን ሲገለጹ በሌላ በኩል ለህብረተሰቡ የሚጠቅሙ አዳዲስ ፈጠራዎች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እየተፈጠረ መሆኑን ይገልጻሉ።
ለዚህ ማሳያ ይሆን ዘንድ ወደ ሀገራችን የመጣችውን ሶፊያን ማንሳት ይቻላል የሰው መሰል አገላለጾችን ማሳየት እና ከሰዎች ጋር መገናኘት የምትችል እውነተኛ ሰዋዊ ሮቦት ያደርጋታል በተጨማሪም የአማርኛን ቋንቋ እንድትናገር ፐሮገራም ተደርጋም አይተናል። ይህ የሚያሳየን የወደፊቱን የቴክኖሎጂ ሳይንስ የታለመለት ለምርምር፣ ለትምህርት እና ለመዝናኛ የተነደፈ የሚል ቢሆንም ነገር ግን የAI ስነ-ምግባር እና ስለ ሮቦቲክስ የወደፊት ሁኔታ ሁነኛ ማሳያ መሆኑዓን ያሳያል።

ጥቅም እና ጉዳቱ
የሚያበረክቱት ጥቅሞች
- በፈለጉበት ሰዓት እና ቦታ ሊገለገሉበት ይችላሉ
- በሽታዎችን በትክክል መመርመር
- ድግግሞሽ ለሆኑ ስራዎች ሳይታክቱ መስራት በብቃት እና በጥራት እረጅም ሰዓት መስራት
- ፈጣንና ቀልጣፋ ስራዎችን ያከናውናሉ
- ውሳኔዎችን በፍጥንት የመወሰንና የማስተላለፍ ብቃት
- ማሽኖች በሽታዎችን በትክክል መመርመር
- ለአየር ንብረት ከመቆጣጠር እና የሚበከሉ ነገሮችን እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል

የሚያስከትሉ ጉዳቶች
- በቀጣሪዎች ተመራጭ መሆን በአነስተኛ ዋጋ በርካታ ስራዎችን መስራት
- የተልየ ፈጠራ ስራዎችን አይፈጠሩም
- ከታለመላቸው አላማ ውጭ አገልግሎት አይሰጠኡም
- ስሜቶችን የመረዳት እና የመግባባት