ኮምፒዩተር ሳይንስ (Computer science

መግቢያ

የኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አስተምሮቱ ስለ የኮምፒዩተር እና ኮምፒዩቲንግ ጥናት፣ ስለ የንድፈ ሃሳባዊ እና አልጎሪዝም መሠረቶቻቸውን፣ ሃርድዌር እና ሶፍትዌሮችን እና መረጃን ለማቀናበር አጠቃቀማቸውን የሚያጠና ሳይንስ ነው።

የኮምፒዩተር ሳይንስ ዲሲፕሊን የአልጎሪዝም እና የመረጃ አወቃቀሮችን፣ የኮምፒውተር እና የኔትወርክ ዲዛይን፣ መረጃን እና የመረጃ ሂደቶችን ሞዴል ማድረግ እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጥናትን ያጠቃልላል።

የኮምፒዩተር ሳይንስ አንዳንድ መሠረቶቹን ከሂሳብ እና ምህንድስና ስሌትና ጥናትን መሰረት ያደረገ እንደ የመጠባበቂያ መስመር ንድፈ ሀሳብ (queueing theory) ፣ ፕሮባቢሊቲ ንድፈ ሀሳብ (Probability Theory) እና ስታቲስቲክስ (Statistics) እና የኤሌክትሮኒክስ ከባቢን የሚያጠቃልል (electronic circuit) ዲዛይን ካሉ ቴክኒኮችን አጠቃሎ የያዘ ሳይንሳዊ ዘርፍ ነው።

የኮምፒዩተር ሳይንስ የአዳዲስ ስልተ ቀመሮችን፣ የመረጃ አወቃቀሮችን እና የኮምፒዩተር ስርዓተ ክፍሎች መገንባት (Computer architectures) በፅንሰ-ሀሳብ ዲዛይን፣ መለካት እና ማሻሻል፣ መላምት፣ ሙከራን ለመተግበር በእጅጉ  ይጠቀማል።

የኮምፒውተር ሳይንስ እንደ አምስት የተለያዩ ግን እርስ በርስ የተያያዙ የትምህርት ዓይነቶች ያለው ቤተሰብ አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡-

  • የኮምፒዩተር ምህንድስና (Computer Engineering),
  • የኮምፒዩተር ሳይንስ (Computer science), 
  • የመረጃ ስርዓት (Information System),
  • የመረጃ ቴክኖሎጂ (Information Technology) and
  • የሶፍትዌር ምህንድስና (Software engineering).

የኮምፒዩተር ሳይንስ ዋና ንዑስ ክፍሎች (The major subfields of computer science)

የኮምፒዩተር ሳይንስ ዋና ዋና ንዑስ መስኮች የሆኑትን የጥንት አስተምሮቶችን ጨምሮ ስለ የኮምፒዩተር ስነ-ምህዳር ፣ የፕሮግራም ቋንቋዎች እና የሶፍትዌር መገንባትን ያካትታል። ይሁን እንጂ የሂሳብ ሳይንስ (የሳይንሳዊ መረጃዎችን ለመቅረጽ የአልጎሪዝሚክ ዘዴዎችን ይጠቀማል)፣ ግራፊክስ እና የረቀቀ እይታን፣ የሰው-ኮምፒውተር ግንኙነት፣ የመረጃ ቋትና የመረጃ ስርዓት፣ የኔትዎርክ እና ከኮምፒዩተር ሳይንስ ተግባር ጋር ብቻ የሚተያይባቸው ማህበራዊና ሙያዊ ጉዳዮችንም ያካትታሉ። ከእነዚህ ንዑስ መስኮች መካከል አንዳንዶቹ እንደ ባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) እና የሒሳብ ኬሚስትሪ (computational chemistry) ካሉ ሌሎች ዘመናዊ መስኮች ጋር ይዛመዳሉ። እነዚህ ተደጋግፈው የሚደባለቁት የኮምፒውተር ሳይንቲስቶች በመስኩ ውስጥ ያሉትን በርካታ የዲሲፕሊን ግንኙነቶች ለይተው የማወቅና ተግባራዊ በማድረግ በሚያስከትለው ውጤት አዝማሚያ በማየት በማጥናት ተዛማጅ መሆናቸውን ይገልፃሉ።

የኮምፒዩተር ሳይንስ ልዩ ለዩ መስኮች ያሉት ሲሆን ወደ የሚከተሉት 15 ክፍሎች ተዘርዝረው እንመለከታቸውለን፡

  • Algorithms and complexity
  • Architecture and organization
  • Computational science
  • Graphics and visual computing
  • Human-computer interaction
  • Information management
  • Intelligent systems
  • Networking and communication
  • Operating systems
  • Parallel and distributed computing
  • Platform-based development
  • Programming languages
  • Security and information assurance
  • Software engineering
  • Social and professional issues

የኮምፒውተር ሳይንስ አሁንም ጠንካራ የሒሳብና የምሕንድስና መነሻ አለው። የኮምፒዩተር ሳይንስ ባችለር፣ የማስተርስ እና የዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራሞች በየጊዜው ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ጥያቄዎች ይቀርባሉ። እነዚህ ፕሮግራሞች ተማሪዎች እንደ የትኩረት አካባቢያቸው ተገቢውን የሂሳብና የምህንድስና ኮርሶች እንዲያጠናቅቁና መሰረታዊ እውቀቶችን እንዲያዳብሩ ይፈለጋል። ለምሳሌ ሁሉም የምሩቃን የኮምፒዩተር ሳይንስ ዋና የሆነውን ዲክረት ሂሳብ (discrete mathematics, logic combinatorics) እና የአንደኛ ደረጃ ግራፍ ፅንሰ-ሃሳብ ማጥናት አለባቸው። በተጨማሪም ብዙ ፕሮግራሞች ተማሪዎች በጥናታቸው መጀመሪያ ላይ በካልኩለስ፣ በአኃዛዊ መረጃ፣ በቁጥር ትንታኔ፣ በፊዚክስና በምህንድስና መርሆች ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁ ይጠይቃሉ።

እነዚህንም በምስል፣ በድመጽ፣ በጽሁፍ፣ እንዲሁም ማጣቀሻ ሰነዶችና ሳይቶችን በመዘጋጀት ማብራሪያዎችን በማዘጋጀት የምናብራራው እና የምናየው ይሆናል።

About Author

ዮሐንስ ቴክ (admin)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *